Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 124 የሱስ ሆይ ከእኔ ጋር ኑር የዘፈን ግጥሞች
፩፡ የሱስ ሆይ ከእኔ ጋር ኑር
የሚጐዳኝን አባርር።
ዘወትር አንተን ልማጠን
የሱስ ሆይ ከኔ ጋር ሁን።
፪፡ አንተ ከኔ ጋር ከሆንህ
ነፍሴን በጸጋህ ካረካህ
አንዳች አይጐድልብኝም
የሱስ ሆይ ከኔ ጋር ሁን።
፫፡ ከዚች ዓለም ስሰናበት
ካንተ ጋር ልሁን በላይ ቤት።
ላቅርብልህ ውዳሴን
የሱስ ሆይ ከኔ ጋር ሁን።