Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 116 ና ቸር መሐሪ፥ አንተ ሁን የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ና ቸር መሐሪ፥ አንተ ሁን
የበጎችህ እረኛ
አሳየን ቅዱስ ቁስልህን
የቆሰልኸውን ስለኛ።
በደብረ ጽዮን ሰብስበን
በዚያ ነው ደስ የሚለን
በዚያ ካንተ ጋራ።
፪፡ ኦ የሱስ፥ በልባችን ላይ
የፍቅርህን ጐርፍ አፍስስ
የእምነት ጉድለትን ስቃይ፥
የደምህ ኃይል ይፈውስ።
ኦ አንተ ታላቅ ይቅር ባይ፥
ና ለውጥ በፍቅርህ ፀሐይ
ብርዳችንን በሙቀት።