Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 97 ኦ መንፈስ ቅዱስ ና ወደኔ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 97 ኦ መንፈስ ቅዱስ ና ወደኔ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ኦ መንፈስ ቅዱስ ና ወደኔ፤
ልቤንም ክፈት ለአንተ።
በእውነቱ የምትመራ፥
የጨለመ ልቤን አብራ።
፪፡ የኃጢአት ጸጸት ሲሞርደኝ፥
ፍርሃት ጭንቀት ሲያውከኝ፥
ጸንቼ እንድገኝ በቃልህ፥
አትለየኝ በምሕረትህ።
፫፡ ከክፉ ምኞት ነፍሴን አንጻ፥
አኑረኝ በቅድስና።
ጥርጥርም እንዳይገባብኝ፥
በቸርነትህ ጠብቀኝ።
፬፡ ጠማማ ፈቃዴንም አቅና፤
ሰላምህን በልቤ አግባ።
ለአምላክ ክብር ለሰው ጥቅም፥
እርዳኝ ለመኖር በዓለም።

Exit mobile version