መዝሙር 96 መንፈስ ቅዱስ ወደኔ ና የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ መንፈስ ቅዱስ ወደኔ ና፤
በልቤም ውስጥ ብርሃን አብራ፤
በአንተ እንድጸና።
እውነትንም አስተምረኝ፤
የሕይወትን መንገድ ምራኝ፤
ያምላክ ገንዘብ ነኝና።
፪፡ ዘወትር ወደ እውነት ምራኝ፤
ወዳንተ ጠርተህ አቅርበኝ፤
ወንጌልን አስተምረኝ።
ከክፉውም ተለይቼ፥
ከኃጢአቴም ነጽቼ፥
እንድከተልህ እርዳኝ።
፫፡ አቤቱ ጸጋህን ስጠኝ፤
በዘመኔ ሁሉ እርዳኝ፤
በእምነት አንተ አጽናኝ።
በጌታ በየሱስ ክርስቶስ፥
እንድድንና እንድኖር፥
አንተ ረደኤት ሁንልኝ።
፬፡ ሰይጣን እንዳያሸንፈኝ፥
ዓለም እንዳያታልለኝ፥
ዘወትር አንተ ጠብቀኝ።
የአምላክ ልጅ ነኝ በጸጋው፤
ሰርክ ይህንን አስታውሰኝ፤
በእምነቴም አበርታኝ።
፭፡ ስንፍናዬ ይሰማኛል፥
መጸለይም ይሳነኛል፤
አንተ ግን ጸልይልኝ።
መንፈስ ቅዱስ ሆይ በኔ ኑር፤
ድካሜንም አጥፋልኝ፤
ኃይልና ብርታት ስጠኝ።
፮፡ በትዕግሥት፥ በጥበብ
ፍሬ ለማፍራት ለማደግ
ሁልጊዜ አነሣሣኝ።
በተሰጠኝ ቅዱስ መክሊት፥
ዘላለም የማያልቅ ሀብት
እንዳገኝ እኔን እርዳኝ።
፯፡ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፥ አበርታኝ፤
በጭንቀቴም ሁሉ አጽናኝ።
በሞትም ድምፅ ስጠራ፥
እንደ ምእመን እንድሞት፥
አጠንክረኝ በሃይማኖት።
ነፍሴን ጠብቅ አደራ።
