መዝሙር 92 ሕያው የሆነውን አዳኝ አገለግላለሁ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ሕያው የሆነውን አዳኝ አገለግላለሁ
ሕያው የሆነውን የሱስ እመሰክራለሁ።
በምሕረት እጁ ዳስሶ ድምፁን ያሰማኛል
በችግር ጊዜ ረድኤት ይሆነኛል።
ሕያው ሕያው ሕያው ነው ኢየሱስ
ዛሬም ነገም ለዘላለም ከኔ አይለይም።
፪፡ በዚህ ዓለም ሕይወቴ በፍቅሩ ከቦኛል
በድካሜ ሳይለይ ተስፋ ይሆነኛል።
በሕይወት ማዕበል እንኳ ከኔ አይለይም
በሚገለጽበት ቀን ይከሰታል።
ሕያው ሕያው . . .።
፫፡ ክርስቲያች ተደሰቱ ዘምሩ በዕልልታ
ኢየሱስ ንጉሥ ነው ዘምሩ ሃሌሉያ።
ለሁሉ ተስፋ ሰጪ ረድኤት በመከራ
ፍቅሩ ፍጹም ጥልቅ ነው ቸሩ ጌታ።
ሕያው ሕያው . . .።
