Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 91 ፀሐይዋ ጠልቃ መንጋት ሲጀምር የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 91 ፀሐይዋ ጠልቃ መንጋት ሲጀምር የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ፀሐይዋ ጠልቃ መንጋት ሲጀምር
ከመድኃኒቴ ከኢየሱስ ጋር
ሥራዬ አልቆ በሰማይ ልኖር
ፀሐይዋ ጠልቃ ቀን ሲጀምር።
፪፡ ፀሐይዋ ጠልቃ ደመና ሲሄድ
ፍርሃት አይሆንም ደግሞም ሞገድ
ያ የደስታ ቀን ያለም ፍጻሜ
ይነጋልኛል ለዘለዓለም።
፫፡ ፀሐይዋ ጠልቃ በእጁ ሲመራኝ
ወዳባቴ ቤት ሊያደርሰኝ
አብን አይቼው ሲያነጋግረኝ
ለዘለዓለም ሳይለየኝ።
፬፡ ፀሐይዋ ጠልቃ ሙታን ሲነሡ
ደግሞ እንደገና ላያለቅሱ
በመልካምዋ አገር አንለያይም።
አብረን ልንኖር ለዘለዓለም።

Exit mobile version