መዝሙር 90 የአምላክ ልጆች ደስ ይበለን የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የአምላክ ልጆች ደስ ይበለን
ሞትን አሸንፎ የሱስ ተነሥቶአል።
የከበቡትን ጠላቶች ድል ነሥቶ
በሞትና በሲኦል ላይ ነገሠ።
፪፡ የታሰረውን የግር ብረት ሰበረ
በክብር ሊያኖረን እኛን ለማዳን።
መላእክትም ለርሱ መዝሙር ዘመሩ
አዳኙ ተነሥቶአል ደስ ይበላችሁ።
፫፡ አምላክን በመዝሙር እናመስግን
የተሰጠን መንፈስ ታላቅ ነውና።
ሕይወታችንን በደስታ ለማርካት
ተስፋችንን በርሱ እንድናጸና።
፬፡ የሱስ የኃዘንን ጨለማ አጠፋ
የሰማያዊ ክብሩን ሊያካፍለን።
ድል ስለነሣ ደስ ይበለን
ሞትን አሸንፎ የሱስ ተነሥቶአል።