Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 86 በትንሣኤ ቀን መለከት በሚነፋበት ጊዜ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 86 በትንሣኤ ቀን መለከት በሚነፋበት ጊዜ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ በትንሣኤ ቀን መለከት በሚነፋበት ጊዜ
ዕልልታ ሃሌ ሉያ ይሆናል።
የጌታም ቅዱሳን ከርሱ ጋራ ይደሰታሉ
ዕልልታ ይሆናል።
ዕልልታ ሃሌ ሉያ ዕልልታ አሜን
ይሆናል
ሃሌ ሉያ በትንሣዔ ቀንም ጥዋት
ሙታን ነጻ ሲለቀቁ።
ዕልልታ ይሆናል
ሃሌ ሉያ በዚያን ጧት ይሆናል።
፪፡ በትንሣኤ ቀን ጥዋት ከጌታ ጋራ ስንሆን
ዕልልታ ሃሌ ሉያ ይሆናል።
አባት እናት ወዳጆችን ሁሉ እናገኛለን
ዕልልታ ይሆናል።
ዕልልታ . . .።
፫፡ በትንሣዔኤ ቀን ጥዋት ታላቅ ደስታ ይሆናል
ዕልልታ ሃሌ ሉያ ይሆናል።
ሃሌ ሉያ
መድኃኒቴን አየዋለሁ ለኔ የሞተልኝን።
ዕልልታ ይሆናል።
ዕልልታ . . .።
፬፡ በትንሣኤ ቀን ጌታችንን እናገኘዋለን
ዕልልታ ሃሌ ሉያ ይሆናል።
ወደ ሕይወት ቤታችንም በክብር እንደርሳለን።
ዕልልታ ይሆናል።
ዕልልታ . . .።

Exit mobile version