Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 83 አርነት ወጣን ነጻም ሆነናል የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 83 አርነት ወጣን ነጻም ሆነናል የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ አርነት ወጣን ነጻም ሁነናል
ጌታችን የሱስ ተቤዥቶናል።
ሲኦልን ሻረ ሕዝቡን አዳነ
በገርነትም እንቀበለው።
፪፡ ትልቅ ደስታ ነው አርነት መውጣት
በኢየሱስ ክርስቶስ ነፃነት ማግኘት።
ለየሱስ መሆን እርሱንም ማመን
የዘለዓለም ሕይወትን ማግኘት።
፫፡ የሱስ ሆይ ላንተ ይሁን ምስጋና
ስለ ፈሰሰው ቅዱሱ ደምህ።
ሸክማችን ቀረ ኀዘንም ጠፋ
ሕይወታችን ሁሉ ተሻሻለ።
፬፡ ወደ ቤታችን ወደ አምላካችን
እንሄዳለን እንደ ተስፋው ቃል።
ያረጀ ሥጋን እንተዋለን
አዲስ ሕይወትም እንለብሳለን።

Exit mobile version