Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 79 የሱስ ሆይ በትንሣኤህ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 79 የሱስ ሆይ በትንሣኤህ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ የሱስ ሆይ በትንሣኤህ
ሞትን ድል ነሥተሃል።
እንድናመሰግንህ
ስጠን የመንፈስን ኃይል።
ሞትን አጠፋህልን
የሕይወት ራስ ሆንህልን
በክብርህ ልንኖር።
፪፡ በሞትህ የሰማይ በር
ለኛ ተከፍቶአል።
እኛንም ከመቃብር
ድምፅህ ያስነሣናል።
አንተንም በሕይወቱ
የሚያምንብህ ሰው ሁሉ
መንግሥትህን ይወርሳል።
፫፡ በግርማ ስትመጣ
ሁሉ አንተን ያያል።
ዙፋንህ ሲዘረጋ
ፍርድህ ይፈጸማል።
መለከቱ ሲሰማ
የሞቱት ይነሣሉ
ፍትሕ ይቀበላሉ።

Exit mobile version