Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 75 በመቃብር ተኛ የዓለም መድኅን የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 75 በመቃብር ተኛ የዓለም መድኅን የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ በመቃብር ተኛ የዓለም መድኅን
ሕያው ሆኖ ለኛ ተነሣልን።
ከመቃብር ተነሣ
ጠላታችንን ድል ነሥቶአል
ድል ነሥቶአል ለእኛ ድል
ነሥቶአል።
ለዘላለም ይነግሥልናል በላይ
ተነሣ ተነሣ ሃሌ ሉያ ተነሣ።
፪፡ በከንቱ ጠበቁት ያንን መቃብር
በከንቱ አተሙት ያለቱን በር።
ከመቃብር . . .።
፫፡ ሞትን አሸነፈ መድኃኒታቸን
ሲኦልንም ሻረ አዳኛችን።
ከመቃብር . . .።

Exit mobile version