Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 69 ፈተናን ፈሪ ሰው ሆይ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 69 ፈተናን ፈሪ ሰው ሆይ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ፈተናን ፈሪ ሰው ሆይ
ወደ ጌትሴማኒ ሂድ።
ላንዲት መራራ ሰዓት
ያዳኝህን ሥቃይ እይ።
ከኀዘኑም ሳትርቅ
ከርሱ ጸሎትን ተማር።
፪፡ ወደ ፍርድ ሸንጎ ሄደህ
ጌታህ ሲከሰስ እየው
ታላቁን የሞት ጽዋ
የሱስ ክርስቶስ የጠጣው
ላንተ ሲል ነው ወንድሜ
መስቀሉን ተካፈለው።
፫፡ በቀራንዮ ተራራ
ሄጄ በግሩ ሥር ልውደቅ
ድንቁን ታምር አልረሳም
ያምላክን ቅዱስ መሥዋዕት።
ተፈጸመ ሲል ልስማው
ሞትንም ከርሱ ልማር።

Exit mobile version