መዝሙር 58 በቀረበ ጊዜ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ በቀረበ ጊዜ
የፋሲካ በዓል፥
ጌታን እንዲህ አሉት
ተማሮች ባንድ ቃል።
፪፡ አቤት መምህር ሆይ
ከአብ ዘንድ የመጣህ
ፋሲካን በወዴት
እናዘጋጅልህ?
፫፡ ይህንን ስላሉት
ጌታም አዘዛቸው፥
ሂዱ በፊታችሁ
ታገናላችሁ ሰው።
፬፡ ውኃ ተሸክሞ
ሲሄድ ወደ ጌታው
እንዲህ ብላችሁ
ጠይቁት ያንን ሰው
፭፡ እባክህ አሳየን
የማረፊያ ስፍራ፥
መምህር የሚያርፍበት
ከተማሮቹ ጋር።
፮፡ ያሳያችሁማል
ጥሩውን እልፍኝ፥
ፋሲካን ለመብላት
አዘጋጁልኝ።
