መዝሙር 57 ከኃጢአት የሚያነጻኝ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ከኃጢአት የሚያነጻኝ
የኢየሱስ ደም ብቻ ነው፥
ፍጹም ሰው የሚያደርገኝ፥
የኢየሱስ ደም ብቻ ነው።
ኦ ፍጹም ብሩክ ምንጭ
ኃጢአቴን ያጠበው
ሌላ ምንጭ አላውቅም
የኢየሱስ ደም ብቻ ነው።
፪፡ ይቅርታን የሚሰጠኝ
የኢየሱስ ደም ብቻ ነው፥
ንጹህም የሚያደርገኝ፥
የኢየሱስ ደም ብቻ ነው።
ኦ ፍጹም . . .።
፫፡ ተስፋዬና ሰላሜ
የኢየሱስ ደም ብቻ ነው፥
ጽድቅንም የማገኘው፥
በኢየሱስ ደም ብቻ ነው።
ኦ ፍጹም . . .።
