መዝሙር 564 ክርስቲያኖች ሆይ እንነሣ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ክርስቲያኖች ሆይ እንነሣ
እንገሥግስ በእልልታ
የሱስ ነው ከኛ ጋራ።
መስቀሉንም አንሸከም
ለመከተል ብንደክም
ሳይረዳን አይተወንም።
በቅን መንገድ ይመራናል
ከጉዳት ይጠብቀናል።
፪፡ የሱስ ገባ በጀግንነት
ጦር ወደ ተፋፋመበት
እንከተል በድፍረት።
ለጌታ ሰንደቅ ዓላማ
ተንቀን ብንታይ እንኳ
ከእውነት አንዛባ።
ይፈጸም የንጉሥ ተስፋ
ክብሩም በኛ ይንሰራፋ።
፫፡ አርበኞች ሁነን በፍጥነት
ብንዋጋ ለመሠረት
ባለሙ ቅዱስ እውነት
የሐሰት ምሽግ ይፈርሳል
ክፋት ኃጢአት ድል ይሆናል
የሱስ ብቻ ይነግሳል
ምሕረቱ በሚታይበት
ይሰፋል የወንጌል ትምህርት።
፬፡ ድንቅ ኃያል አምላክ ነው ስሙ
የተሳለ ሰይፍ ነው ቃሉ
ታጠቀ በእውነቱ
በሚገባ ድል ይነሳል
ሁከት በሰላም ይተካል
ሰው ከጥፋት ይድናል።
የሚሠቃይ በባርነት
በርሱ ያገኛል አርነት።
፭፡ አባቶች በእምነት ያዩት
ጻድቃን የተነበዩለት
ሰው ሆኖ ተወለደ
ሕዝቡ እየቀለዱበት
የሞተው በመስቀል እንጨት
በግርማው ይገለጣል
በመስቀሉ ላላፈሩ
ያካፍላል ከክብረቱ።
፮፡ ለግዛቱ እንሰለፍ
በሥራችን አንስነፍ
ቀን በከንቱ አናሳልፍ
ብርሃን በማይጠፋበት
በሰማይ በሚሰጠን ቤት
እናገኛለን ዕረፍት።
ከዚች ምድር ስንሻገር
ዕልል እያልን እንዘምር።
