Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 559 የሱስ ሆይ የሞቀ ፍቅርን ስጠኝ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 559 የሱስ ሆይ የሞቀ ፍቅርን ስጠኝ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ የሱስ ሆይ የሞቀ ፍቅርን ስጠኝ
ፈቃድህን ለመፈጸም አበርታኝ
ለወንጌል ሥራ ትጉ አድርገኝ
መንፈስህ ይምራኝ።
፪፡ በታማኝነት በቅድስናም
እንዳገለግለህ ኃይልህን ስጠኝ
በትዕግሥት መከራን እንድቀበል
አቤቱ አጽናኝ።
፫፡ ባለም ለክብርህ እንድኖር እርዳኝ
ጽኑ የሆነ እምነትን ስጠኝ
ሰላም ዕረፍት በሰማይ አድለኝ
ጉዞን ስንፈጽም።

Exit mobile version