መዝሙር 558 መንጋህን ስታሰማራ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ መንጋህን ስታሰማራ
ለጠፋው ስትራራ
አስበኝ።
በዚህ ዓለም ስንከራተት
ሐሳቤን ወዳንተ ጐትት
ጠብቀኝ።
፪፡ በተወጋው ጐንህ ብቻ
ባንተ በጎች መከማቻ
ሰውረኝ።
ቸር እረኛ ክፈትልኝ
እኔ ደግሞ ያንተ በግ ነኝ፤
ያንተ ነኝ።