መዝሙር 55 አምላክ ለኛ ብሎ ቢያፈሰው ደሙን የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ አምላክ ለኛ ብሎ ቢያፈሰው ደሙን
ፀሐይ ከለከለች ደማቅ ብርሃንዋን።
የከበረው ሥጋ የከበረው ደም፥
በመስቀል ላይ ዋለ ኢየሩሳሌም።
እዩት ኢየሱስን፥ መስቀሉ ማማሩ
ለተመራመረው
ብዙ ነው ምሥጢሩ።
፪፡ ቢገርፉት ቢሰቅሉት ቢያላግጡበት
ምንም አላገኙም ከርሱ ዘንድ ስሕተት።
ፈጣሪ መሆኑን ምሥጢሩ ገብቷት፥
ጌታን አልይዝም አለች ግዑዟ መሬት።
እዩት . . .።
፫፡ ይኼ ታላቅ ንጉሥ ሲገለጥ ከሰማይ
የናቁት የወጉት ይሉለታል ዋይ ዋይ።
ምድርና ሰማይ ከፊቱ ሲሸሹ
ወዴት ልግባ ይላል ትልቁ ትንሹ።
እዩት . . .።
፬፡ ወደ ላይ ያረገው የከበረው ሥጋው፥
ዳግመኛ መምጣቱን ሁላችን አንዘንጋው።
በሰማይ ለሚኖር ቅዱስ አባታችን፥
ምስጋና ይድረሰው ከኛ ከሁላችን።
እዩት . . .።
