Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 547 ሰው በጭንቅ በደስታም ቢኖር የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 547 ሰው በጭንቅ በደስታም ቢኖር የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ሰው በጭንቅ በደስታም ቢኖር
የሞቱ ቀን ይደርሳል።
በዓለሙ የትም ቢዞር፥
ከመሞት አያመልጥም፤
ሊመርጥም አይችልም።
ጊዜው ከደረሰ፥
መመለስ አይሆንለትም፤
ምድራዊ ተስፋው ፈረሰ።
፪፡ ግን በየሱስ የሚያምን
ወደ ሰማይ ይሄዳል።
በመሬት ውስጥ ቢቀበርም፥
በሰማይ ዘውድ ያገኛል።
ብፅዕናን መርጦአል፤
አይወሰድበትም።
በየሱስ ሞት ጸድቆአል፤
የሰማይ ርስቱን ይወርሳል።

Exit mobile version