መዝሙር 546 ኦ መድኃኒታችን የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ኦ መድኃኒታችን
ኦ የክብር ንጉሥ
ኦ ታላቅ ጠባቂያችን
ዘመን ሲለዋወጥ
አንተ ሥሉስ ቅዱስ
ለዘላለም አትለወጥም።
እናክብር ስምህን።
ነፍስ ያላቸው ሁሉ
ድንቅ ሥራህን ያውሩ።
፪፡ ኦ የቆሰልህልን
ርኅሩኅ ንጉሣችን
ስለኛ የተሰቀልኸው
አንተ ትሰጣለህ
ኃይል በድካማችን።
ኦ መድኅን ተመስገን።
ውዳሴ ስብሐትም
ያቅርቡልህ ሁሉም።
