መዝሙር 540 የሱስ ልጆቻችንን የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የሱስ ልጆቻችንን
ወዳንተ ስናቀርባቸው
አምነን ቅዱስ ተስፋህን
በስምህ ስናጠምቃቸው
በፍቅርህ ተቀበላቸው
በረከትህንም ስጣቸው።
፪፡ የሱስ ክርስቶስ ያንተ ደም
በአብ ፊት ይቀድሳቸው።
መንፈስ ቅዱስ በቃልህ
በሕይወት መንገድ ይምራቸው።
ጽድቅህን ይጎናጸፉ
መንግሥትህንም ይውረሱ።
፫፡ ታናናሾች በጎችህ
ከእረኛቸው አይለዩ።
ሁልጊዜ በመንገድህ
ሄደው ካለም ሸር ይዳኑ።
ርስትህ እንዳይቀርባቸው
አንተ ራስህ ጠብቃቸው።
