Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 54 የሱስ ሆይ፥ በመስቀል ላይ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 54 የሱስ ሆይ፥ በመስቀል ላይ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ የሱስ ሆይ፥ በመስቀል ላይ
በመሠቃየትህ፥
የዘላለም ነፃነት
ለሁሉ አስገኘህ።
መስቀልህ፥ መስቅልህ፥
ለሁሉ ኃይል ሆነ።
ነፍሴ ምሕረት ካገኘች፥
በሰላም ታርፋለች።
፪፡ በመስቀልህ አጠገብ
ነፍሴ ስትጨነቅ፥
ግሩም የደኅንነት ብርሃን
በልቤ ይፈንጥቅ።
መስቀልህ . . .።
፫፡ ኦ የሱስ የአምላክ በግ፥
ሰላምህን ስጠኝ።
ከዚህ ዓለም መከራ
ሁልጊዜ ታደገኝ።
መስቀልህ . . .።

Exit mobile version