Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 538 የሱስ ክርስቶስ ርኅሩኅ መድኅኔ ሆይ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 538 የሱስ ክርስቶስ ርኅሩኅ መድኅኔ ሆይ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ የሱስ ክርስቶስ ርኅሩኅ መድኅኔ ሆይ፥
ወዳጄና አዳኜ ነህ።
በረከትህን እንድትሰጠኝ
ነው የምናፍቀው ዘወትር።
መድኃኒቴ እናፍቅሃለሁ
አንተን ለማየት እቸኵላለሁ።
ጌታዬ ሆይ፥ ጌታዬ ሆይ
ላይህም እቸኵላለሁ።
፪፡ ያለም ደስታ እንዳያታልለኝ፥
ቸር አምላኬ ሆይ፥ ጠብቀኝ።
ሁልጊዜ ከኔ ጋር እንድትኖር
ነው የምናፍቀው ዘወትር።
መድኃኒቴ . . .።
፫፡ ፍቅርህም ጥልቅ ነው ከባሕር ይልቅ፤
በርሱ አሳርፈኝ ካለም ጭንቅ።
የሱስ በፊትህ ሞገስ እንዳገኝ
ነው የምናፍቀው ዘወትር።
መድኃኒቴ . . .።
፬፡ የሱስ ከሁሉ እወድሃለሁ
ስለኔ ሞተሃልና።
ወደ ሰማይ ቤት እንድታደርሰኝ
ነው የምናፍቀው ዘወትር።
መድኃኒቴ . . .።

Exit mobile version