መዝሙር 535 ወንጌል የሚለውን ሰምቼ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ወንጌል የሚለውን ሰምቼ
ደስታዬ በዝቶአል።
አምላኬ ርስት ስለ ሰጠኝ፥
ምስጋናዬ ልቋል።
የአምላክ ልጅ ተዛምዶናል፤
ወንድማችንም ሆኖአል፤
ደስታዬ በዝቶአል።
፪፡ ምድራዊ ችግር ድካምም
በጣም ቢበዛብኝ፤
የልቤ ተስፋና ሰላም
ሁሉም ቢጠፋብኝ፤
ግን አምላክ በሰማይ ዙፋን
ሲሰጥ ለወንድሜ ሥልጣን
ደስታዬ በዝቶአል።
፫፡ ይህ ያምላካችን ምክር ነው፤
የጸጋ ምስጢርም።
የአምላክ ልጅ ቤዛችን ነው፤
አፍስሷል ደሙንም።
ኦ ግሩም የሆነ መድኅኔ
ሲሞት ጠፋልኝ ዕዳዬ፤
ደስታዬ በዝቶአል።
፬፡ ያዳምን ጉድለት በባሕርዬ
ስወርሰው ታሰርሁ፤
በክርስቶስ ግን በመድኀኔ
አርነት ወጣሁ።
የአምላክ ልጅ ሰው ሆኖልኝ
ነፍሱን ሰጥቶ አዳነኝ፤
ደስታዬ በዝቶአል።
፭፡ እንዲህ ከሆነ ማመንን
ልተው አልደፍርም።
ያቀረበውንም መሥዋዕት፥
ልንቀው አልችልም።
ኃጢአቴ ቢበዛብኝም፥
ይበልጣል ግን የክርስቶስ ደም፤
ደስታዬ በዝቶአል።