Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 534 ኦ የሱስ በትንሣኤህ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 534 ኦ የሱስ በትንሣኤህ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ኦ የሱስ በትንሣኤህ
ሞትና ድል ነሥተሃል።
እንድናመሰግንህ
ስጠን የመንፈስ ኃይል።
ሞትን አጠፋህልን
የሕይወት ራስ ሆንህልን
በክብርህ ልንኖር።
፪፡ በሞትህ የሰማይ በር
ለኛ ተከፍቶአል።
እኛንም ከመቃብር
ድምጽህ ያስነሣናል።
አንተንም በሕይወቱ
የሚወድህ ሰው ሁሉ
ሰማይን ይወርሳል።
፫፡ በግርማ ስትመጣ
ሁሉ አንተን ያያል።
ዙፋንህ ሲዘረጋ
ፍርድህ ይፈጸማል።
ሲሰማ መለከቱ
የሞቱት ይነሣሉ
ፍርድ ይቀበላሉ።

Exit mobile version