መዝሙር 527 የገና ቀን ደስታችን ነው የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የገና ቀን ደስታችን ነው
የሱስ የመጣለት፥
መላእክት ሌሊት ዘመሩ
ኮከቡን አበራልን።
፪፡ የቤተልሔም ታናሽ ሕፃን
ግሩም ንጉሥ ሆኖአል፤
የሰማይ ደስታ ሊሰጠን
ወደኛ ወርዶአል።
፫፡ አሁን በሰማይ በአብ ቤት
በክብር ይኖራል፤
ግን ጸሎታችንን በሌት
በቀንም ይሰማል።
፬፡ በገና ቀን ደስ ይለናል
ከፍ ባለ ምስጋና፤
ሕፃኑም ደስታን ይሰጠናል፤
ለርሱ ሃሌ ሉያ።
፭፡ የሱስ የመጣ ዕለት ማታ
ታላቅ ብርሃን ታየ፤
እረኞችም በችኰላ
መጡ ወደ ጌታ።
፮፡ ያ ኮከብ ያበራል ገና
ብናምን ያምላክን ቃል
ይሰጣል የሰማይ ደስታ
ለሕይወት ይመራል።
፯፡ የሰማይ ሰራዊት ሁሉ
በደስታ ዘመሩ፤
ሰላም ለዓለም በሙሉ
ይሁን እያሉ።
፰፡ ኦ ኢየሱስ እኔን እርዳኝ
ላንተ እንድዘምር፥
በእጅህም እኔን ምራኝ፤
ልኑር ላንተ ክብር።
