Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 522 ከየሱስ ጋር የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 522 ከየሱስ ጋር የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ከየሱስ ጋር ትራመዳለህ ወይ
ትእዛዛቱንስ ትጠብቃለህ ወይ
የሱስ ከላይ የላከው ፍቅሩ ይደርስሃል ወይ
ሕይወትህን የሱስ ይመራል ወይ?
የሱስ ይመራል ወይ የሱስ ይመራል ወይ
አሳብህን መንገድህን በሙሉ
የሱስ ይመራል ወይ የሱስ ይመራል ወይ
ሕይወትህን የሱስ ይመራል ወይ?
፪፡ ስትጸልይ ልብህ ይደሰታል ወይ
ብቻህን ካምላክ ጋር ስትነጋገር
ና ተከተለኝ ብሎ መድኃኒትህ ሲጠራህ
ሕይወትህን የሱስ ይመራል ወይ?
የሱስ ይመራል ወይ . . .?
፫፡ ነፍሳትን ወደ አምላክህ ለማምጣት
ዞትር በጸሎት ትተጋለህ ወይ
በፈተና በርትተህ በየሱስ ድል ለመንሣት
ሕይወትህን የሱስ ይመራል ወይ።
የሱስ ይመራል ወይ . . .?

Exit mobile version