Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 521 አንድ ገዢ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 521 አንድ ገዢ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ አንድ ገዢ ወደ የሱስ በሌት መጣ
ስለ ጽድቅ ብርሃን ጠይቆ ሊረዳ
ጌታም አስተማረው ግልጽ በሆነ መንገድ
ዳግመኛ ተወለድ (3)
እኔ እውነት እውነት እነግርሃለሁ
ዳግመኛ ተወለድ።
፪፡ የሰው ልጅ ሆይ፥ ቃሉን ከልብ አድምጠው
ከየሱስ ክርስቶስ አፍ ነው የሚፈልቀው
ለአንተ ይህ ቃል በከንቱ አይውረድ።
ዳግመኛ ተወለድ …።
፫፡ ልትገባ ብትወድ ወደ ክብሩ እረፍት
ከዳኑት ጋራ ልትዘምር ባንድነት
ይህም ድንቅ ሕይወት እንዲገኝ ካንተ ዘንድ።
ዳግመኛ ተወለድ …።
፬፡ ልብህ ለማየት የሚናፍቀው
በሰማይ ደጃፍ እየጠበቀህ ነው
ከዚያም ያን ውድ መዝሙር ልትሰማ ብትወድ።
ዳግመኛ ተወለድ …።

Exit mobile version