Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 517 ጸጋዬ ይበቃሃል የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 517 ጸጋዬ ይበቃሃል የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ጸጋዬ ይበቃሃል ሲል ጌታ
ምንኛ ታላቅ ስጦታ ሰጠነ።
ኃይሉ በድካማችን ተገልጾ
ትምክህታችን በርሱ ብቻ ይሆናል።
የሚመካ በአምላክ ኃይል ይመካ።
፪፡ ጸጋው ለደከሙ ኃይል ይሰጣል
ጸጋው ለምስኪኑ አለኝታ ነው።
ጸጋው ኀዘንተኛውን ያጽናናል
ጸጋው በነፃ ለሁሉ ተሰጥቶአል።
የሚመካ . . .።
፫፡ ጸጋው የኃጢአት ቀንበር ይሰብራል
ጸጋው ለጭቁኖች ነጻነት ያውጃል
ጸጋው በሙላት ሰላም ያሰፍናል
ጸጋው ሙሉ ደስታ ያትረፈርፋል።
የሚመካ . . .።
፬፡ በራሳችን ኃይል እንዳንመካ
ጌታ ገልጾ ቃሉን አስተምሮናል
ብንዝል ብንደክም በማይሻር ቃሉ
በድካማችን ይፈጸማል ኃይሉ።
የሚመካ . . .።

Exit mobile version