Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 515 ወንጌልን ላልሰሙ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 515 ወንጌልን ላልሰሙ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ወንጌልን ላልሰሙ መናገር አለብኝ
ጌታ የሱስን ለማያውቁት
የፍቅሩንም ነገር ከቶ ላልቀመሱት
ጣፋጩን ታሪክ ልንገራቸው።
ቃሉ ላልደረሰው
መናገር አለብኝ
የዓለም ሕዝብ ሁሉ
ማዳኑን እንዲያውቁ።
፪፡ ችግር ወዳለበት ቦታ ተልኬያለሁ
ምቾት ፍጹም ወደሌለበት፤
ዓለም ሁሉ እንኳን እንደሞኝ ቢቈጥረኝ
ጌታን ካሰደስትኩ ይበቃኛል።
ቃሉ . . .።
፫፡ ከጌታ የራቁ ብዙ በጎች አሉ
መልእክቱን የምትነግሯቸው፤
ንቃ ሁሉን ነገር ወደ ኋላ ተወው
ቃሉ ወዳልደረሰው አምራ።
ቃሉ . . .።

Exit mobile version