Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 514 አዳነኝ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 514 አዳነኝ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ አዳነኝ አዳነኝ በጣም ደስ ብሎኛል
ክብሩ ይስፋ ምስጋናም ይድረሰው
ሊያድነን ራሱን ሠዋ ነፃነት አጐናጸፈን
ነፃነት አጐናጸፈን።
ድነናል ድነናል አዲስ ሕይወት እንጀምር
ድነናል ድነናል ለዘላለም ልንኖር
የየሱስ ደም አንጽቶናል
ፍቅሩንም አሳይቶናል
ከኃፍረትም አድኖናል
አዳነን ክብሩ ይስፋ።
፪፡ አዳነን አዳነን በቃሉ መሠረት
ሰላም ደስታ ዕረፍትንም ሰጠን
የኃጢአትን ስርየት ሰጠን
እዳችንንም ከፍሎታል
እዳችንንም ከፍሎታል።
ድነናል . . .።
፫፡ አዳነን አዳነን በርሱ ውስጥ እንድንኖር
ሃሌ ሉያ ከርኩሰት አዳነን
ለዘላለም በነፃነት
ለክብሩ እንዘምራለን
ለክብሩ እንዘምራለን።
ድነናል . . .።

Exit mobile version