መዝሙር 510 ደስ ይበለን የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ደስ ይበለን ጨለማ አልፎአል
የጽድቅ ብርሃን ተተክቶአል።
የእግዚአብሔር ልጅ ታላቅ መድኅን
አማኑኤል ደረሰልን።
አማኑኤል አማኑኤል አማኑኤል
እግዚአብሔር ከኛ ጋር ነው።
፪፡ የምሥራች ደስታ ስሙ
አዳኝ መጥቷል ለሰው ሁሉ
እውነት መንገድ ሕይወት እርሱ
እንድትድኑ በእርሱ እመኑ።
አማኑኤል …።
፫፡ አማኑኤል የእኛ ተስፋ
ለእኛ ብሎ ክብሩን አጣ።
በእርሱ መሞት እኛ ዳንን
በቁስሎቹ ተፈወሰን።
አማኑኤል …።
፬፡ ደስ ይበለን መድኅን መጥቶአል
ካባቱ ጋር ሊያስታርቀን
እርቅ ሆነልን ሰላም ደስታ
አማኑኤል ክብሩ ይስፋ።
አማኑኤል …።
፭፡ የሰው ልጆች ደስ ይበለን
አማኑኤል ለእኛ አለን።
እናክብረው እንወድሰው
ለውለታው ክብር እንስጠው።
አማኑኤል …።