መዝሙር 506 ትውስ ሲለኝ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ትውስ ሲለኝ የጌታዬ ፍቅር
ያደረገልኝን በጐልጐታ።
ካገር ወዳገር በመንከራተት
ፀሐይና ውርጭ ሲፈራረቁበት።
ይሁዳ ሽጦት ጴጥሮስ ሲክደው
ተከታዮቹም ጥለውት ሲሸሹ።
የፊጥኝ ታስሮ ለፍርድ ሲነዳ
ጥፊውና ግርፉ ሲወርዱበት።
ትዝ ይለኛል ያ መደኅኔ
በእንጨት ላይ የሞተው ስለእኔ።
ትውስ ይለኛል የመስቀል ፍቅሩ
ያደረገልኝ ውለታ ሁሉ።
፪፡ አልራሩለትም አስረው ሲገርፉት
ያን መልከ መልካም ርህሩህ ፈጣሪ
የማይችለውን መስቀል አስይዘው
መድኅናቸውን ለፍርድ ሲወስዱት።
ሲጮህ ሲያነባ በጣር ተከቦ
በደም ላብ ባሕር ሆኖ ሲያነባ
ሲወድቅ ሲነሳ አባ አባት ሲል
ተሠቃየለኝ ነፍሱ እስክትዝል።
ትዝ ይለኛል . . .።
፫፡ ይረሳኛል ወይ ያ የጣር ጊዜ
መድኃኒቴን የተሳለቁበት።
ከመስቀል ውረድ ራስህን አድን
እያሉ ጠላቶች ሲያሾፉበት።
ጨለማ ውጦን የነበርነውን
እኛን ለማዳን ከክብሩ ወርዶ።
የዓለምን ኃጢአት ያስወገደውን
ታላቁን መድኅን ነፍሴ አትረሳውም።
ትዝ ይለኛል . . .።
