መዝሙር 505 ሕፃን ተወልዶልናልና የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ሕፃን ተወልዶልናል
ወንድ ልጅም ተሰጠን፤
ፈጣሪ ከፍጥረቱ ጋር
ተዛመደን።
ወልድን ላከልን
እንዲሆን አዳኛችን
ምሕረቱን ለሰጠን
ይሁን ምስጋናችን።
፪፡ አዳም በውድቀቱ
ላወረሰን ኃጠአት
መድኃኒት ተገኘ
በእንስሶች በረት።
ኃጢአታችንን
ሊያስወግድልን
ሰው ሆኖ ተወለደ
መድኃኒታችን።
፫፡ እስረኞችን ሁሉ
አወጣ አርነት
ከሞት ከቅጣትም
አወጀ ነፃነት።
ጠላቶቹን ሁሉ
በኃይል ድል ይነሣል
ለኃጢአተኞች
ይቅርታን ይሰጣል።
፬፡ በበረት ግርግም ውስጥ
የተኛውን መድኅን
ሰው እንደሚገባው
ማመስገን አይችልም።
በውርደቱ ክብሩ ተገልጦ
ባይታይም
የማዳኑን ሥራ
ፈጽሞአል ላለም።
፭፡ ለእኛ ብፅዕናን
በፍቅሩ ይሰጣል፤
በቃሉም የጸጋ
ፈቃዱን ይገልጻል።
ስጦታውን ለግሶ
ለሁሉ ሲሰጠው
ልባችንን አጽንተን
ቸል አንበለው።
፮፡ በእምነት ተቀብለን
እንስገድለት፤
እንዲህም እያልን
እንዘምርለት።
በምድር ተወልደህ
መድኅን የሆንህልን
ኦ ቸር ወንድማችን
ኦ አምላክ ተመስገን።
