መዝሙር 503 ሰላም አለኝ ሁሉም አለኝ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ሰላም አለኝ ሁሉም አለኝ
ሰላም አለኝ በልቤ፥ በልቤ፥
ቅዱስ ቃሉን አንብቤ፥
ደኅንነት አግኝቻለሁ፥
ስሞት ወደ ጌታ እሄዳለሁ።
፪፡ በየሱስ ደም በየሱስ ደም
ታጠበልኝ ኃጢአቴ፥ ኃጢአቴ
ተለወጠ ሕይወቴ፥
በወንጌል እጸናለሁ፤
ስሞት ወደ ጌታ እሄዳለሁ።
፫፡ እረፍት አለኝ፥ እረፍት አለኝ፥
እረፍት አለኝ በየሱስ፥ በየሱስ፥
የማይጠፋ ደስታ፥
የማይናወጥ ተስፋ፥
በሕይወቴ በጣም ተስፋፋ።
፬፡ ተለወጥኩኝ፥ ተለወጥኩኝ፥
ተለወጥኩኝ በየሱስ፥ በየሱስ፥
አዲስ ፍጥረት ሁኛአሁ፥
መንፈሱን አግኝቻለሁ፥
ስሞት ወደ ጌታ እሄዳለሁ።
፭፡ ኅዘን የለም፥ ጭንቀት የለም፥
ፍርሃት ጠፍቷል ከልቤ፥ ከልቤ፥
መንፈሱ ያጽናናኛል፥
በደስታ ሞልቶኛል፤
ጌታ ዞትር ይጠብቀኛል።
፮፡ ላመስግው፥ ላመስግነው፥
ላመስግነው ጌታዬን፥ ጌታዬን፥
በመስቀል ተሠቃይቶ
ከፈለልኝ ዕዳዬን፥
ክብር ክብር ለስሙ ይሁን።
