Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 501 ስራመድ ስጓዝ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 501 ስራመድ ስጓዝ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ስራመድ ስጓዝ በፀሐይ ብርሃን
በረግረግ ውስጥ በተራራም ላይ።
የሱስ ብሎኛል ከቶ አልተውህም፥
በማይወድቀው በጽኑ ተስፋው።
የሰማይ ብርሃን የሰማይ ብርሃን፥
ነፍሴን ያበራል በክብሩ ኃይል።
ሃሌ ሉያ እደሰታለሁ
እዘምራለሁ ለኢየሱስ።
፪፡ የሞት ጨለማ ጥላውን ቢያጠላ
ከአዳኙ ሊለየኝ አይችልም።
ጨለማ አያውቅም ፍጹም ብርሃን ነው፥
ሁሉንም ትቼ ልከተለው።
የሰማይ ብርሃን . . .።
፫፡ ቶሎ ልገሥግሥ በፀሐይ ጮራ
እንድኖር በአስደሳች ስፍራ።
እየዘመርኩኝ የአምላኬን ፍቅር፥
እኖራለሁኝ ያለ ችግር።
የሰማይ ብርሃን . . .።

Exit mobile version