Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 50 የሞተልኝ ጌታዬን የሱስን ሳስበው የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 50 የሞተልኝ ጌታዬን የሱስን ሳስበው የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ የሞተልኝ ጌታዬን የሱስን ሳስበው
በጣም ያስደንቀኛል
ምን ዓይነት ፍቅር ነው?
ምን ዓይነት ፍቅር ነው?
ምን ዓይነት ፍቅር ነው?
በቀራንዮ ኮረብታ ለኔ የገለጽከው።
ምን ዓይነት ፍቅር ነው?
ምን ዓይነት ፍቅር ነው?
በቀራንዮ ኮረብታ ለኔ የገለጽከው።
፪፡ ስለ ሞተልኝ የሱስ
ለመናገር ፍቅሩን፥
ይቸግራል ላንደበት
አልችለውም ፍጹም።
ምን ዓይነት . . .።
፫፡ በመስቀል ተቸንክረው
እጆችና እግሮችህ፥
ተቀጣህ በኃጢአቴ፥
መርገምን ተሸክመህ።
ምን ዓይነት . . .።
፬፡ ኃጢአት ሳይኖርብህ
ቅዱስ የኔ ጌታ፥
ስለ ኃጢአቴ ነው
የሞትክ በጐልጐታ።
ምን ዓይነት . . .።
፭፡ ጌታ የሱስ ክርስቶስ ሆይ
ያለም ሁሉ አዳኝ፥
አስደናቂ ፍቅርህን፥
እንዳስበው እርዳኝ።
ምን ዓይነት . . .።

Exit mobile version