Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 498 ጌታን ስንከተል የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 498 ጌታን ስንከተል የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ጌታን ስንከተል
በቃሉ ድንቅ ብርሃን፥
ብፅዕናን ክብርን ይሰጠናል።
በየሱስ ብናምን፥
በኛ ውስጥ ይኖራል፥
እንታዘዘው እናክብረውም።
እንመነው እንገዛለትም
ሌላ መንገድ አይገኝም፥
የሚሰጥ ሰላምን።
፪፡ ችግር ቢበዛብን
ፍርሃትም ቢይዘን፥
ፍቅሩ ነው ሁሉን የሚገዛ።
ለሥቃይና ሞት፥
ራሱን ሰጠ ቤዛ፥
ስለዚህ ለርሱ እንገዛ።
እንመነው . . .።
፫፡ ሁሉን ብንታገሥ
ብንችል መከራን፥
በኢየሱስ እናሸንፋለን።
ታግሦ እስከ ሞት፥
አጠፋው ኃጢአትን፥
ስለዚህ እንጽና በእምነት።
እንመነው . . .።
፬፡ በፍቅሩ ደስታን
ይወዳል ሊሰጠን፥
ለእርሱ እንስጥ ልባችንን።
ምሕረትን ደስታንም፥
ጸጋንና ፍቅርን፥
ከቶ ለማይወዱት አይሰጥም።
እንመነው . . .።
፭፡ ነጽተን ከኃጢአት
በቅዱስ አንድነት፥
እንኖራለን በሰማይ ቤት።
አምላክን አክብረን፥
ስንኖር በዕረፍት፥
እናቀርባለንም ምስጋና።
እንመነው . . .።

Exit mobile version