Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 493 አንተ ምስኪን ኃጢአተኛ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 493 አንተ ምስኪን ኃጢአተኛ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ አንተ ምስኪን ኃጢአተኛ
ያን ጽኑ ተስፋ አገኘህ ወይ?
ከችግር ሁሉ የሚያወጣህ፥
ደራሽ መድኅንስ አለህ ወይ?
እኔስ ከመድኅኔ ጋር መድኅኔ መድኀኔ
እኔስ በመድኀኔ በጽኑ ተስፋው
አርፌአለሁ።
፪፡ ልብህም ሲያዝንብህ
ከንቱው ደስታ ሲጠፋብህ።
የትኛው ቃል ነው የሚያጽናናህ፥
ማነው ሐቀኛ ጓደኛህ?
እኔስ ከመድኀኔ . . .።
፫፡ ንብረትህ ሁሉ ሲጠፋ
የምትሆነውንም ስታጣ።
ተስፋ ስትቆርጥ ስትጨነቅ፥
የሚያጽናናህ አለህ ወይ?
እኔስ ከመድኀኔ . . .።
፬፡ ስማ አንተ ወንድሜ ሆይ
የጌታን ቃል ብትመረኰዝ፥
ያዳኙን ጸጋ ብትቀበል፥
ሙሉ ደስታ ታገኝ ነበር።
እኔስ ከመድኅኔ ጋር መድኅኔ መድኀኔ
ክብር ለመድኀኔ ብፁዕ ነው
የሱስን ያመነ።

Exit mobile version