Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 491 ሰላም እንደ ወንዝ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 491 ሰላም እንደ ወንዝ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ሰላም እንደ ወንዝ በመንገዴ ሲወርድ፡
ኃዘን ቢመጣ እንደ ማዕበል።
የሆነ ቢሆን ካንተ ተምሬአለሁ፥
ሕይወቴ ሰላም ነው እላለሁ።
ሰላም ነው በልቤ
ሰላም ነው ሰላም ነው በልቤ።
፪፡ ጠላት ቢነሣ ፈተናም ቢመጣ፡
በአምላኬ ተስፋ ልጽና።
ደካማነቴን ጌታ አውቆአልና፥
ደሙን አፍስሶ አድኖኛል።
ሰላም ነው . . .።
፫፡ ኃጢአቴ በመስቀል ተቸነከረ፡
በሙሉ ተደመሰሰ።
ሸክሜን ላነሣልኝ ምስጋና ይሁን፥
ነፍሴ ሆይ ጌታን አመስግኚ።
ሰላም ነው . . .።
፬፡ ጌታ ሆይ መምጣትህን አፋጥነው፡
ደመናውን አስወግደው።
ጌታ ይመጣል መለከት ይነፋል፡
ያን ጊዜ ነፍሴ ደስ ይላታል።
ሰላም ነው . . .።

Exit mobile version