መዝሙር 490 ልባችሁ አይታወክ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ልባችሁ አይታወክ
በእግዚአብሔር እመኑ
በኔም እመኑ፤
ባባቴ ቤት እኔ በምኖርበት
እንድትሆኑ።
እመጣለሁ ወደኔ ልወስዳችሁ፥
መንገድ እውነት ሕይወትም እኔ ነኝ።
፪፡ እውነት እውነት በኔ የሚያምን ሁሉ
ሥልጣን አለው፤
እኔ በአብ አብም በእኔ እንዳለ
ካመናችሁ፥
በስሜ የምትለምኑት ሁሉ
አብ እንዲከብር እፈጽመዋለሁ።
፫፡ ብትወዱኝ ትእዛዛቴን ጠብቁ
በኔ እመኑ፤
የእውነት መንፈስ ከናንተ ይኖራል
ሊያጸናችሁ።
በስሜ የሚመጣው ቅዱስ መንፈስ
አጽናኝ እርሱ ያስተምራችኋል።
፬፡ ሰላሜን እተውላችኋለሁ
እንዳትፈሩ፤
ሰላሜንም እሰጣችኋለሁ፥
በእርሱ ጽኑ፥
እሄዳለሁ ተመልሼ እመጣለሁ፥
ልባችሁ አይታወክ በኔ እመኑ።
