መዝሙር 485 አምላክህ ለፍርድ ቢመጣብህ አሁን የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ አምላክህ ለፍርድ ቢመጣብህ አሁን
ተዘጋጅተህ ትገኝ ይሆን ወይ?
የፍርድ መለከትስ ቢነፋ አሁን?
ምን አሳብ ይይዝህ ይሆናል?
እንዴትስ ያን ድምጽ ትሰማለህ?
፪፡ ባላሰብኸው ወቅት በማይመስልህ ሰዓት
ያ ቀን እንደ ሌባ ይመጣል።
ለጻድቃን ደስታ ለኃጥአን ኃዘን፥
ጌታችን በፍርዱ ይሰጣል።
ላንተስ ምን ይሰጥህ ይሆናል
፫፡ በጎችን በቀኝ ፍየሎችን በግራ
አድርጎ መንጋውን ይለያል።
አንተንስ ከበጎቹ ጋራ ይጥራ
ወይስ ስፍራህን የት ላይ ያሳያል?
በየት ትቆማለህ በፍርዱ?
፬፡ በጎቹን በፍቅር እናንተ ቡሩካን
እያለ በገነት ያስገባል።
ለኃጥአን ግን ሂዱ እናንተ ርጉማን
ብሎ መቅሠፍትን ይሰጣል
አንተንስ ምን ይልህ ይሆናል
፭፡ ካምላከህ ጋር ልትገናኝ ተዘጋጅ
የሱስን ለማወቅ ተጋደል።
አሁን ለሁላችን ምሕረቱን ሲሰጥ
ጊዜ ሳያልፍብህ ተቀበል
የጸጋን ጊዜ አታባክን።
