Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 481 የክርስቶስ ወታደር የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 481 የክርስቶስ ወታደር የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ የክርስቶስ ወታደር በርታ ተራመድ
የየሱስን መስቀል ከፊት አስቀድም፥
ክርስቶስ የሱስ ይምራ ጠላት ይሸነፍ፥
ሰንደቅ ዓላማህን ጸንተህ ተመልከት።
የክርስቶስ ወታደር በርታ ተራመድ
መስቀሉን አስቀድም አንተ ተከተል።
፪፡ ድልህ በክርስቶስ ነው ጠላት ይጠፋል
ክርስቲያን ጠንክር በርታ ሲኦል ያከትማል
ካሸናፊው ጋራ ባሸናፊው ኃይል፥
ባንድ ሐሳብና እውነት ወደፊት ቀጥል።
የክርስቶስ ወታደር . . .።
፫፡ ቤተ ክርስቲያን ትጽና ድል ትጎናጸፍ
ክርስቲያን ተመራ በሀይማኖት መንገድ።
በወንድሞች ፍቅር በኅብረት ጸንተን
እንሂድ ወደፊት ኃይሉን ተላብሰን።
የክርስቶስ ወታደር . . .።
፬፡ እንሂድ ወደፊት በደስታ መንፈስ
ይቅረብ ዝማሬአችን ለጽድቁ ንጉሥ።
ላሸናፊው ይሁን ክብር ምስጋና፥
መንግሥቱን እንውረስ ከክርስቶስ ጋራ።
የክርስቶስ ወታደር . . .።

Exit mobile version