Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 48 አዳኜ ደሙ ፈሰሰ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 48 አዳኜ ደሙ ፈሰሰ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ አዳኜ ደሙ ፈሰሰ
መድኅኔ ሞተልኝ።
እርሱ ራሱን አዋረደ
እኔን ሊያድነኝ።
በመስቀል በመስቀል
ብርሃንን አገኘሁ
የልቤ ሸክም ተወገደልኝ።
በእርሱ ነው እምነትን ያገኘሁ።
በዚህ ደስታዬን እገልጻለሁ።
፪፡ የተሠቃየው መድኅኔ
ስለኔ ኃጢአት ነው።
ሕይወት ሊሆንልኝ ለኔ
አምላክ ልጁን ሠዋው።
በመስቀል በመስቀል . . .።
፫፡ ያምላክ ልጅ በታላቅ ፍቅሩ
ሕይወቱን ሠዋልኝ።
የርሱ ወገን ሊያደርገኝ
አፈሰሰ ደሙን።
በመስቀል በመስቀል . . .።
፬፡ እንባዬ ሲፈስ በኀዘን
ዕዳዬን አይከፍልም።
ግን ኢየሱስን በማመን
እድናለሁ ፍጹም።
በመስቀል በመስቀል . . .።

Exit mobile version