Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 479 ተነሡ ምእመናን የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 479 ተነሡ ምእመናን የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ተነሡ ምእመናን ስሙ መለከት
ሰይፉን አዘጋጅቶአል ሊያጠፋን ጠላት።
ውጊያውን አፋፍሞአል እጅግ ያስፈራል
የእግዚአብሔር ዕቃ ጦር ግን ድል ይነሣል።
ተነሡ ታጠቁ እንሂድ ወደፊት
ሊያሰናክል ተዘጋጅቶአል ጠላት።
ምእመናን እንገሥግስ ታጥቀን
በእምነት፥
አሸናፊው የሱስ አለ ከፊት።
፪፡ ተዘጋጅተን እንኑር ዘወትር እንትጋ
ነቅተን እንጠብቅ የጌታን ዓላማ።
በኢየሱስ በማመን ልባችን ይጽና፥
ድላችን እርሱ ነው ይግባው ምስጋና።
ተነሡ ታጠቁ . . .።
፫፡ ጠላትን የማይዋጋ አክሊል የለውም
ሽንፈት የጠላት ድል ግን የኢየሱስ ነው።
በእምነት ለጸና ኃይል የሚሰጠው
አሸናፊው ጌታ መድኃኔዓለም ነው።
ተነሡ ታጠቁ . . .።

Exit mobile version