Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 47 የሱስ ሆይ፥ ለእኔ ሰላም የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 47 የሱስ ሆይ፥ ለእኔ ሰላም የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ የሱስ ሆይ፥ ለእኔ ሰላም
ልትሰጠኝ ሞተሃል
በሥቃይና በሕማም
ነፍሴን አድነሃታል።
ከጥፋት አሁን ድኛለሁ፤
ሕይወትንም እወርሳለሁ።
ይሁንልህ ውዳሴ፤
ጌታ ኢየሱስ አምላኬ።
፪፡ ስለ መራራው ሕማምህ፥
ልቤ ያመሰግናል።
በሥቃይ በድካምህ፥
ሕይወት ተገኝቶልኛል።
ልትሰርይ የኔን በደል፥
ሞትን ቀምሰሃል በመስቀል።
ይሁንልህ ውዳሴ፤
ጌታ ኢየሱስ አምላኬ።

Exit mobile version