Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 466 አመልካለሁ ይህንን ታላቅ ጌታ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 466 አመልካለሁ ይህንን ታላቅ ጌታ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

አመልካለሁ ይህንን ታላቅ ጌታ፥
አመልካለሁ በማንም የማይረታ።
አመልካለሁ ግንበኞች የናቁትን
አመልካለሁ የማዕዘን እራስን።
፩፡ የእውቀት እራስ የጥበብ ጌታ
ምንም ቢፈተን የማይረታ።
በሰው አእምሮ አይገመትም፥
ወርዱም ስፋቱም አይዘለቅም።
አመልካለሁ . . .።
፪፡ ፍቅሩን አይቼ ቀምሼዋለሁ
ፍጹም ላመልከው ቃል ገብቻለሁ።
በመከራዬ እርሱ እየገባ
ይጋፈጠዋል እንዳልረታ።
አመልካለሁ . . .።
፫፡ ጥፋቴን ሁሉ በፍቅር እያየ
ያሳልፈኛል ልጄ እያለ።
ከሁሉ በፊት ፍቅሩ ሰብሮኛል
በመስቀሉ ላይ ነፍሱን ሰጥቶኛል።
አመልካለሁ . . .።
፬፡ ከእርሱ ሌላ ወዳጅ የለኝም
እንደ እርሱ የሚሆን ከቶ አላገኘም።
የውስጥ ችግሬን ሳልነግረው ያውቃል
ለእኔ ሲከብደኝ ይሸከመዋል።
አመልካለሁ . . .።

Exit mobile version