መዝሙር 463 ምስጋና ለእግዚአብሔር ይድረሰው የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
ምስጋና ለእግዚአብሔር ይድረሰው
ስለማይነገር ጸጋው።
የወንጌል ብርሃን አንጸባርቆአል፥
ጊዜውም ደርሶአል።
የውዳሴ ዘመንም ሁኖአል፥
ተስፋችን ጽኑ ነው በክርስቶስ ወንጌል።
ነቅተን እንጠብቅ ሙሸራውን ለመቀበል፥
ምስጋና ለእግዚአብሔር ይሁነው፥
ስለማይነገር ጸጋው።