Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 459 መከሩን ሁሉ የሚጠብቁ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 459 መከሩን ሁሉ የሚጠብቁ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ መከሩን ሁሉ የሚጠብቁ
ሰብሳቢዎች ወዴት ይገኛሉ?
ለጌታ ሥራ የሚሠሩ፥
በእውነት ለጌታ የሚገዙ?
ማን ይላካል? ማን ያገልግል?
የጌታን መልእክት፥
ማን ያደርስለታል?
ስለ ቃሉ ማን ይተጋል?
የሕይወት አክሊልን እንዲያገኝ።
፪፡ በከተማዎች በገጠሮችም
በሁሉ ይገኛል መልካም ሰብል።
ሰዓቱ ሳያልፍ ታጠቁ ንቁ፥
ነፍሳትን ሁሉ ለማዳን ትጉ።
ማን ይላካል? . . .።
፫፡ የመከሩ ጌታ ተዳርሶአል
የጌታን ሰብል ሁሉ ሰብስቡ፤
ስለ ድካማችሁ ተደስቱ፥
የደስታን አክሊል ተጐናጸፉ።
ማን ይላካል? . . .።

Exit mobile version