Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 458 በጥዋት እንዝራ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 458 በጥዋት እንዝራ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ በጥዋት እንዝራ የወንጌል ፍሬ
በንጋትም ሆነ በድቅድቅ ጨለማ፤
መከሩን እንጠብቅ የአጨዳን ጊዜ፥
በደስታ ነዶውን እንሰበስባለን።
ነዶውን እንሰብስብ ነዶውን እንሰብስብ
በደስታ ነዶውን እንሰበስባለን፤
ነዶውን እንሰብስብ ነዶውን እንሰብስብ
በደስታ ነዶውን እንሰበስባለን።
፪፡ በፀሐይ አንዝራ በጨለማ ጊዜ
ሰይጣንን አንፍራ ሠራዊቱንም፤
ቀስ በቀስም ያልቃል የዓለም ሥራችን፥
በደስታ ነዶውን እንሰበስባለን።
ነዶውን እንሰብስብ . . .።
፫፡ በልቅሶም እንኳ ቢሆን ለጌታ እንዝራ
ብዙም ቢጠይቅ መከራ ቢበዛ፤
ልቅሶአችንም ያልፋል ከጊዜ በኋላ፥
በደስታ ነዶውን እንሰበስባለን።
ነዶውን እንሰብስብ . . .።

Exit mobile version